Monday, September 22, 2025

ኒውዮርክ ለፍልስጤም መንግሥት እውቅና የሚሰጡ ሀገራት ቁጥር እየጨመረ ነው

ኒውዮርክ   ለፍልስጤም መንግሥት እውቅና የሚሰጡ ሀገራት ቁጥር እየጨመረ ነው 🇯🇴🇯🇴


ዛሬ በፈረንሳይና በሳዑዲ አረብያ በተጠራው ጉባኤ ላይ አንዳንድ የዓለም ሀገራት መሪዎች ዛሬ ለፍልስጤም እንደ መንግሥት እውቅና ይሰጣሉ ተብሎ እየተጠበቀ ነው። እስራኤል ይህን እርምጃ የጋዛውን ጦርነት በሰላማዊ መንገድ የመጠናቀቅ እድልን የሚያበላሽ ስትል አስጠንቅቃለች። በኒውዮርክ የሚካሄደው ይኽው ጉባኤ የፍልስጤማውያንን ሞራል ከፍ ሲያያደርግ በመሬት ላይ ግን ለውጥ ያመጣል ተብሎ አይጠበቅም። ከሀማስ ሚሊሽያዎች ጋር ውጊያ ላይ ያለው እጅግ ቀኝ አክራሪ የሚባለው የእሥራኤል መንግስት በእስራኤል ታሪክ የፍልስጤማውያን መንግስት አይኖርም ሲል አስታውቋል። 

እስራኤልና ዩናይትድ ስቴትስ ራሳቸውን ጉባኤው እንደሚገሉ ተዘግቧል። በተባበሩት መንግሥታት የእስራኤል አምባሳደር ዳኒ ዳነን ጉባኤውን የሰርከስ ትርዒት ሲሉ አጣጥለዋል። ብሪታንያ ካናዳ እና አውስትሬሊያ ትንናት ለፍልስጤም መንግሥት እውቅና ሰጥተዋል።  ፈረናሳይ እና ሌሎች አምስት ሀገራት ከተመድ ጠቅላላ ጉባኤ በፊት በሚካሄደው ፈረንሳይና ሳዑዲ አረቢያ በጠሩት በዚህ ጉባኤ ላይ በይፋ ለፍልስጤም መንግስት እውቅና ይሰጣሉ ተብሎ ይጠበቃል።

አብዛኛዎቹ የአውሮጳ ሀገራት ለፍlseሴም እውቅና በሰጡበት በአሁኑ ጊዜ ጀርመንና ጣሊያን በቅርቡ ለፍልስጤም መንግስት  እውቅና የመስጠት ምልክት አላሳዩም ። ጀርመን በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ወቅት ለተጨፈጨፉ አይሁዳውያን ሃላፊነት በመውሰዷ የእስራኤል ጠንካራ ደጋፊ ናት። አሁን ግን የእስራኤል ፖሊሲ ክፉኛ እየተቸች ነው። ጀርመን ለፍልስጤማውያን እውቅና መስጠቱ ፣ በሁለት መንግስታት መፍትሔ የሚያስማማ የፖለቲካ ሂደት ማብቂያ ላይ ሊሆን ይገባል ስትል በአጽንኦት ትናገራለች።  የጀርመን መንግስት ቃል አቀባይ ዛሬ እንደተናገሩት እስራኤል በኃይል በያዘችው ግዛት ውስጥ ተጨማሪ በኃይል መያዝ ሊኖር አይገባም ብለዋል።

✳️✳️✳️✳️✳️✳️✳️✳️✳️✳️✳️
©️ 2025 Fankim Post 🔅 ፈንኪም ፖስት 

Friday, September 19, 2025

Sudaanitti haleellaa diroonii Masjiida irratti raawwatameen 78 ajjeefaman

Sudaanitti haleellaa diroonii Masjiida irratti raawwatameen 78 ajjeefaman

 

 


Sudaan bulchiisna Daarfuur keessatti haleellaa diroonii Masjiida irratti raawwatameen yoo xinnaate namoonni 78 ajjeefamuu maddi wallaansa fayyaa onaanoon tokko BBCtti himan.

Haleellaan guyyaa Jimaata har'aa magaalaa el-Faashar keessatti raawwatame kanaaf himannaan Humnoota Deeggarsa Saffiisaa (RSF) irratti kan dhiyaate yoo ta'u, garichi garuu itti gaafatamummaa hin fudhanne.                                                                                                

RSF fi waraanni biyyattii erga wal waraanuu eegalanii amma waggaa lamaa ol lakkoofsiiseera.

Gareen RSF wayita magaalaa el-Faashar guutummaan to'achuuf waraana gaggeessaa jiran kanatti eddoowwan dabalataa qabataa jiraachuun himameera.                                                   

Magaalaan kunis waraana biyyattiitiif Daarfuur keessatti bakka itti deeggara cimaa qabuufi bakka lammiileen nagaa 300,000 ol sababii waraanaatiin itti danqamaniidha.                        

Jiraatoonni tokko BBCtti akka himeetti haleellaa sa'aatii salaataatti raawwatameen            battalumatti namoota hedduu ajjeesse.                                                                                                      

Maddi wallaansa fayyaa tokkoo ammoo namoonni 78 ajjeeffamanii 20 miidhaaan irra gahuu dubbachuun, ammalleen reeffa jijjigaa gamoo jalaa baafamaa jiraachuu dabaluun himan.

BBC Verify ammoo suuraa reeffa namoota 30 uffataan maramee dhiheenya masjiidichaa kan lixa magaalatiitti argamu mirkanneeffachu danda'eera.                                                             

RSF torban kana haleellaa El-Faashar kan waggaadhaan oliif marsee ture irratti akka haaraatti haleellaa bane. Gabaasaaleenis haleellaan kunis kaampii bakka ummanni buqqa'e keessa dahatu Abu Shouk dabalate akka raawwatamu himan.                                                              

Akka Yunivarsitiin Yaaleetti Laaboraatoorii Qorannoo Namoomaa (HRL) kan waraanaa to'atuutti, suuraaleen saataalaayiti gareen RSF amma kaampp irra caalaa akka to'ate akka agarsiisu.                                                                                                                                                    

Akka kutaa kanaatti suuraaleen saatalaayitii akkasumas Waajira Mummee Humna Walii, kan gareewwan hidhaattoota waraanaa Sudaan waliin hiriiranii seeneera.                               

Waajirri mummeen kunis dallaa UN duraanii keessatti kan argamu yoo ta'u, innis sarara murteessaa ittiisaa akka ta'etti yaadama ture.                                                                                       

BBC Verify suuraalee loltoonni RSF gamoo sana keessa jiraachuu agarsiisuu kan mirkanneesse yoo ta'u, garuu guutummaan to'achuufi hiisuun ifa miti.

Gareen kun tobana cimaa dhufuun isaanii buufata xiyyaara el-Faashar fi waajira mummee kutaa waraanaa akka kallattiin haleellaa RFS keessa galu taasisan.

Akka Laaboraatorii Qorannoo Namoomaa kanatti waraanni biyyatti deebiisee yoo humnasaa hin cimfanne magaalaan el-Faashar harka RSF galu dandeessi.

 

Gabaasni kan BBC ti



2025 Gursum Post

Wednesday, September 17, 2025

ኤርትራዊው ስደተኛ ከዩኬ እንዳይባረር ያቀረበው አቤቱታ በፍርድ ቤት ተቀባይነት አገኘ


                    ኤርትራዊው ስደተኛ ከዩኬ እንዳይባረር ያቀረበው አቤቱታ በፍርድ ቤት ተቀባይነት አገኘ


ከሁለት ዓመት በፊት ከኢትዮጵያ ወደ አውሮፓ የተጓዘው ኤርትራዊ ዩናይትድ ኪንግደም በሕገ ወጥ መንገድ መግባቱን ተከትሎ ከአገር እንዲባረር የተወሰነውን ውሳኔ በመቃወም ያቀረበው አቤቱታ ተቀባይነት አገኘ።

በአነስተኛ ጀልባ እንግሊዝ የገባው ኤርትራዊው ዩናይትድ ኪንግደም ከፈረንሳይ ጋር ባደረገችው "አንድ ማስገባት፤ አንድ ማስውጣት" ስምምነት ከአገር የመውጣት ሂደቱ በጊዜያዊነት ታግዷል።

ፈረንሳይ እና ዩኬ በፈረሙት በዚህ ስምምነት መሠረት በጀልባ ወደ አገር ውስጥ የሚገቡ አንዳንድ ስደተኞች ወደ ፈረንሳይ ሲመለሱ፤ ዩናይትድ ኪንግደም ደግሞ ተመጣጣኝ ቁጥር ያላቸውን ጥገኛ ጠያቂዎች የደኅንነት ፍተሻ አድርጋ ትቀበላለች።

25 ዓመቱ ወጣት ባለፈው ሐምሌ ዩናይትድ ኪንግደም እና ፈረንሳይ በደረሱት በዚህ ስምምነት መሠረት ረቡዕ ወደ ፈረንሳይ ለመመለስ ቀጠሮ ተይዞለት ነበር።

በለንደን ከፍተኛ ፍርድ ቤት የቀረበው የኤርትራዊው መዝገብ የዚህ ስምምነት የመጀመሪያው ሕጋዊ አቤቱታ ሲሆን፤ ጠበቃው የዘመናዊ ባርነት ተጎጂ ሊሆን እንደሚችል እና ለዚህም ማስረጃ ለማቅረብ ጊዜ ያስፈልገዋል ሲል ተከራክሯል።

እግዱ የአየር በረራ የተቆረጠላቸው ሌሎች ስደተኞችም ተመሳሳይ መከራከሪያ በማቅረብ ከአገር እንዳይወጡ ለማድረግ አሊያም ለማዝግየት ሊጠቀሙበት ይችላል የሚል ጥያቄን አስነስቷል።

የአገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስትር ጠበቆች ኤርትራዊው ስደተኛ ፈረንሳይ ጥገኝነት መጠየቅ ይችላል ሲሉ ተከራክረዋል።

ስደተኛው ከአገር እንዳይወጣ የተጣለው ጊዜያዊ እግድ የመመለሻ በረራ የተዘጋጀላቸው ሌሎች ስደተኞች ተመሳሳይ አቤቱታ እንዲያቀርቡ እንደሚያበረታታ እና እየጨመረ የመጣውን የአነስተኛ ጀልባዎች ፍልሰት ለመከላከል በሕዝቡ ዘንድ አመኔታ ይሸረሽራል ሲሉ አክለው ተሟግተዋል።

በፍርድ ቤቱ ችሎት የአገር ውስጥ ጉዳይ ባለሥልጣናት ኤርትራዊው የባርነት ሰለባ ስለመሆኑ አቤቱታውን ውድቅ አድርገዋል።

ዳኛ ጀስቲስ ሸልደን ስደተኛው በፈረንሳይ ቤት አልባ እንደሚሆን እና ችግር ላይ እንደሚወድቅ ጠቅሶ ያቀረበውን አቤቱታ ውድቅ ቢያደርጉም፤ የሕገ ወጥ ዝውውር አቤቱታውን ተከትሎ ከአገር እንዲወጣ የሚያስገድደውን ውሳኔ በጊዜያዊነት እንደሚያግዱ ገልፀዋል።

"ከሰዎች ዝውውር አቤቱታ ጋር በተገናኘ መታየት ያለበት አሳሳቢ ጉዳይ አለ፤ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሯ በሕጋዊ አካሄድ ምርመራ አድርገዋል ወይስ አላደረጉም የሚለው መታየት አለበት" ብለዋል።

"ስደተኛው ከፈረንሳይ ሳይሆን በሰው አዘዋዋሪዎች እጅ ወድቆ ስለመሆኑ አሳማኝ ጥርጣሬ ከነበረ፤ ቢያንስ ለአጭር ጊዜ ከአገር እንዳይባረር እግድ መጣል ይቻላል" ሲሉም አክለዋል።

ዳኛው የኤርትራዊው የፍርድ ቤት መዝገቡ እንዲዘጋ ጠበቃው 14 ቀናት ውስጥ ማስረጃ እንዲያቀርብ አዝዘዋል።

የአገር ውስጥ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ለቢቢሲ መንግሥት በስምምነቱ መሠረት የመጀመሪያዎቹ ተመላሾች በአስቸኳይ እንዲመለሱ እንደሚፈልግ እና ጊዜያዊ እግዱ ፖሊሲውን በሰፊው ለማስፈፀም እንደማይከለክል ተናግረዋል።

የተቃዋሚው ወግ አጥባቂዎች ፓርቲ መሪ የሆኑት ኪሚ ዳዲኖች "ነግረናችሁ ነበር" ሲሉ የእግዱን ዜና በተመለከተ አስተያየት ሰጥተዋል።

"አገራችንን በመሠረታዊነት በአገራቸው በመጠኑም ቢሆን እንኳ ደስተኞች ያልሆኑ የማንኛውም ስደተኞች አገር እያደረግናት ነው" ሲሉ ተችተዋል።

የሪፎርም ፓርቲ መሪ ናይጅል ፋራጅ ፖሊሲው ቢሰራ እንኳ የስደተኞችን ቁጥር "አንድ ማስገባት፤ አንድ ማስወጣት" ስርዓት በእንግሊዝ ቻናል የሚደረግን ፍልሰት መቀነስ አይቻልም ብለዋል።

በለንደን ከፍተኛ ፍርድ ቤት በቀረቡ ሰነዶች የስደተኛው ስም ለሕጋዊ አካሄድ ሲባል ያልተጠቀሰ ሲሆን፤ ኤርትራዊው ከሁለት ዓመት በፊት ከኢትዮጵያ ወደ አውሮፓ በመጓዝ .. ሚያዚያ 2025 ጣሊያን ደርሷል።

ከወር በኋላ በቀይ መስቀል እና በሌሎች እገዛ ሲኖርበት ከነበረው ፈረንሳይ እናቱ ለአዘዋዋሪዎች በከለችለት 1,400 ዶላር የእንግሊዝ ቻናልን ተሻግሮ ዩናይትድ ኪንግደም ገብቷል።

2025 ዓመት ብቻ በአነስተኛ ጀልባዎች 30 ሺህ የሚበልጡ ስደተኞች የእንግሊዝ ቻናልን ተሻግረው ዩኬ ገብተዋል።

"የአንድ ማስገባት፤ አንድ ማስውጣት" ስምምነት ባለፈው ሐምሌ በጠቅላይ ሚኒስትር ኪር ስታርመር እና በፈረንሳዩ ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን ይፋ ተደርጓል።

በዚህ ስምምነት በአነስተኛ ጀልባዎች ተጉዘው ዩኬ የሚገቡ ስደተኞችን ፈረንሳይ መልሳ ለመውሰድ እና የጥገኝነት ጥያቄያቸውን ውድቅ ለማድረግ ተስማምተዋል።



2025 RAADIYOO FANKIM